Skip to content

Resources Jokes

Amharic Jokes ቀልዶች

Short, funny Ethiopian jokes in Amharic, most of them short enough to pass on. Some are one line, some are a small scene with two people talking. Search them, read one at a time, or take one away as a card.

One of 210

አንድ የዋህ ጀለስ አለኝ ። ባገባ በአራተኛው ወር ሚስቱ ወለደችና ግራ ተጋብቶ ከሚስቱ ጋ ለመወያየት ወሰነ

ባል፦ አንቺ አጭበርባሪ እንዴት ዘጠኝ ወር ሳይሞላሽ ወለድሽ?

ሚስት፦ አንተ እኔን ካገባህ ስንት ወርህ ነው?

ባል፦ አራት ወር ተኩል

ሚስት፦ እኔ አንተን ካገባሁ ስንት ወር ነው?

ባል፦ አራት ወር ተኩል

ሚስት፦ አንድላይ ሲደመር ስንት ይሆናል?

ባል፦ ዘጠኝ ወር

ሚስት፦ አሁንስ ገባህ?

ባል፦ “ፈጣሪ ሆይ ይቅር በለኝ በወንጀል ጠረጠርኩሽ” ብሏት እቅፍ አረጋት

210 jokes

All jokes

  • አንድ ጊዜ አለቃ ከወዳጃቸው ጋር መንገድ ሲሄዱ፤ ወዳጃቸው ፈሱን ጠረር ሲያረግ ሰምተው ኖሮ እንዴት እንደሚነግሩት እያስቡ እያለ ድንገት ሰውየው «መቼ ነው ወደ ከተማ የመጡት» ቢላቸው «በጠረርርር ……. ሄጄ በታህሳስስ ተመለስኩ» አሉ ይባላል።

  • መምህሩ ክፍል ገብቶ “እስኪ እራሱን ሰነፍ አድርጎ ሚያስብ ይነሳና ይቁም!” ሲል ማንም አልተነሳም። መምህሩ ደገመና “እርግጠኛ ነኝ እዚህ አካባቢ ሰነፎች አይጠፉም” ከማለቱ አንዱ ተማሪ ተነሳና ቆመ። መምህሩም የቆመውን ተማሪ “እሽ እራስህን ሰነፍ አድርገህ ትቆጥራለህ?” ብሎ ሲጠይቀው፤ ተማሪው ቀበል አርጎ “አይ መምህር እንደዛ ሳይሆን ብቻህን ስትቆም ቅር ብሎኝ ነው።” አለው ይባላል።

  • ካንዷ ቆንጆ ጋር ፌስቡክ ላይ ለረጅም ሰዓት ስንፀፃፍ ቆይተን ስልክ ቁጥር ስጠይቃት ስልክ የለኝም አለች። ቆይ ፌስቡክ ምትጠቀመው በ calculator ነው ማለት ነው?

  • አንዱ ሱቅ ይሄድና "ሰላም ነው፤ አስታወስከኝ?" ይለዋል ባለሱቁን። እኔ እጃ "ፊትህ አዲስ አልሆነብኝም" ይላል ባለሱቁ። ሰውየውም "የዛሬ አመት የፍቅረኛሞች ቀን ኮንዶም ስጠኝ" ስልህ ጨርሻለሁ ያልኸኝ ሲለው፤ አዎ "አሁን አስታወስኩህ" ይላል ባለሱቁ። ከዚያ ሰውየው ቆጣ ብሎ "በል አሁን ዳይፐር ስጠኝ" አለው አሉ።

  • ልጅ ወላጅ አምጣ ተብሎ ፤ አስተማሪው እና አባት እየተነጋገሩ ነው

    አስተማሪ : በልጅዎ ቦርሳ ውስጥ ሀሺሽ አግኝተናል

    አባት : እውነት?! በጣም ያሳዝናል!

    አስተማሪ : አዎ! ጉዳዩ አሳሳቢ ነው!

    አባት : በጣም! በጣም አሳሳቢ ነው! ይሄ ደነዝ እስካሁን አልሸጠውም ማለት ነው!

  • አለቃ ሚስታቸው ወይዘሮ ማዘንጊያን ባንድ ደስታ በሚባል ሰውየ ይጠረጥሯቸው ነበር። ታዲያ አቶ ደስታ በድንገት ህይወቱ ያልፋል። አለቃም የአቶ ደስታን ሞት ሲሰሙ "አይ ደስታዬ! አይ ደስታዬ!" እያሉ በአሽሙር ሙሿቸውን አወረዱ ይባላል።

  • አስበሽዋል 3 ሰዓት ሙሉ ሜካፕ ተቀብተሽ ፊትሽን ትቶ መቀመጫሽን ሲያይ ፤ ግን አንተስ አስበኸዋል 3 አመት ሙሉ ብረት ገፍተህ ደረትህን ትታ ኪስህን ስታይ

  • አንዱ የዋህ በዝናብ ሲጓዝ አዳልጦት ይወድቃል። ወድቆ እያለ ብልጭ ይላል ፤ ይኼኔ ምን ቢል ጥሩ ነው “ምነው ፈጣሪ ሳልዘጋጅ ፎቶ አነሳኸኝ”

  • በኢንጂነሪንግ ተመርቀህ ካሜራ ማኑ እስቲ ፈገግ በል ሲልህ “እሱን ስራ ሳገኝ አይሻልም”

  • ሚስት ፡ ውዴ ግን እንደዚህ ደሃ መሆንህን ባቅ ኖሮ አላገባህም ነበር

    ባል ፡ "ህይወቴ አንቺ ነሽ ፤ አንቺ ብቻ ነው ያለሽኝ" ስልሽ ምን መስሎሽ ነበር ታዲያ?

  • በመጨረሻም ተለያየን ፤ እሷም የራሷን ወንድ አገኘች ፤ እኔም እራሴን አገኘሁ

  • ከአምስት አመት በፊት በአንድ የግል ትምህርት ቤት ውስጥ ፈተና ተሰረቀና ሲታረም ሁሉም ተማሪዎች 100% አመጡ፡፡ ወላጆች ውጤቱን አዩና ምን ቢሉ ጥሩ ነው? “ይኼን ፈተና ያረመው ምርጫ ቦርድ ነው እንዴ?”

  • አንዱ ጅል የሀብታም ልጅ ጠብሶ "ስልኬ ጠፋብኝ" ሲላት "እኔ ገዛልሀለሁ በቃ" ስትለው ምን ቢላት ጥሩ ነው "ጫማ ልገዛ በእግሬ ስሄድኮ ነው በተቀደደው የሱሪ ኪሴ ሾልኮ የጠፋው" ብሏት እርፍ። - ይኼ እንከፍ ሱሪና ጫማም ሊያስገዛ

  • “ለወጡም እዘኑለት አንዳንዴ ደረቅ ጉረሱለት” አለች ሽሮ

  • ተበድሮ የደገሰው ሰርግ ላይ አንዱ ስድስት ቁርጥ እንጀራ ሲያነሳ ፤ ሙሽራው ተናዶ “እንዳይሻግትብህ ወንድሜ ” ብሎት እርፍ

  • “መንግስትና ተሳፋሪ ሊወርዱ ሲሉ ነገር ነገር ይላቸዋል” አለ ወያላ

  • የዋኋ ሠራተኛ በሩን በርግዳ ትገባና "ጌታዬ፡ ማድቤቱ በእሳት ተያይዟል" ትለዋለች። ባለቤትየው ገስግሶ ማድቤቱ ሲደርስ መለስተኛ እሳትና ምድጃው ላይ ተጥዶ የሚንተከተክ ድስት ሙሉ ውሃ ያያል። በዚህ ጊዜ ተናዶ "አንች ደደብ፡ ወደኔ ከመምጣት ይልቅ የሚፍለቀለቀውን ውሃ አታፈሽበትም ኖሯል?" በማለት ቢገስጻት "ጌታዬ ውሃው እኮ የፈላ ስለሆነ አያጠፋውም ብዬ ነው" ብላ መለሰችለት አሉ።

  • የፍቅረኛዬ ስልክ ቁጥር ቢጠፋኝ ጓደኛዬ በቃሉ ነገረኝ

A little Ethiopia, every day

Each morning, today’s date in the Ethiopian calendar. Later in the day, a proverb, a recipe, a riddle or a quiz question. Free, on our Telegram channel.

Join on Telegram