Resources Proverbs
Ethiopian Proverbs
Sayings in Amharic, of two kinds. The classical proverbs — ምሳሌ — are the short, fixed ones repeated for generations. The modern sayings are longer and newer, closer to an aphorism than a proverb. Search either, or read one at a time.
Modern one of 506
ከራስህ ጋር ማነጻጻር ያለብህ ብቸኛው ሰው የትናንትናው አንተን ነው506 sayings
All sayings
Modern
ወንድምን በማጥፋት የሚጀመር ጉዞ የሚጠናቀቀው ራስን በማጥፋት ነው
Modern
በግ ህይወቱን ሙሉ ተኩላን ሲሸሽ ይኖርና በመጨረሻ ግን ባመነው ባሳዳጊው ይበላል
Modern
በአንባገነኖች ሀገር የጀግና ቤቱ እስር ቤት ነው
Classical
ሂድ አትበለው እንዲሄድ አድርገው
Modern
በ 1 ዓመት ውስጥ 10 ጓደኛ መያዝ ቀላል ነው፤ ለ 10 ዓመት ከ 1 ጓደኛ ጋር መዝለቅ ግን ድንቅ ነው
Classical
ዝም ባለ አፍ ዝንብ አይገባም
Modern
ከትናንት ይማሩ ዛሬን ይኑሩ ለነገ ተስፈኛ ይሁኑ
Modern
የሚያጠቁህን ጠላቶች ሳይሆን የሚያቅፉህን የውሸት ጓደኞች ፍራ
Modern
ማንም ሰው ላይ በጣም አትተማመን ምክንያቱም የራስህ ጥላ እንኳን ጨለማ ውስጥ ይለይሀል
Classical
ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል
Classical
የቸገረው እርጉዝ ያገባል
Modern
"በሌቦች ብልጽግና እንዳልቀና፣ በክፉ ሰዎች ተድላም እንዳልጎመጅ አግዘኝ" ብሎ ፈጣሪን መማፀን ብልህነትም ልባምነትም ነው
Modern
ጨለማን ጨለማ አያጠፋውም ጨለማን ማጥፋት የሚችል ብርሀን ብቻ ነው፤ ጥላቻንም ጥላቻ ሊያጠፋው አይችልም ፍቅር እንጂ
Modern
ሳያስቡ ከመኖር እያሰቡ መሞት ይሻላል
Modern
ትልቁ ፈተና ሰው ሆኖ መፈጠር አይደለም ሰው ሆኖ መኖር እንጂ
Classical
የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ
Modern
ዳገት በሆነ ህይወት ወደ ፊት እየሄድክ ካልሆነ ወደ ኋላ ትመለሳለህ
Modern
ዛሬ በውሸታሞች የተዋሸኸው ውሸት ስሜትህን ከመጉዳትም አልፎ ነገ እውነተኛ ሰዎችን እንዳታምን ያደርግሃል
Modern
ሰላማዊ ህይወት ለመኖር መሰናበት ያለብህ ሰዎች አሉ
Modern
አለም በጥሩ ሰዎች ተሞልታለች ፤ አንዱንም ማግኘት ካልቻልክ ግን አንዱ ሁን
Modern
ሰዎች አንተን ማዳመጥ ካቆሙ ፤ አንተም ለእነሱ ማውራትህን አቁም
Classical
ለአኩራፊ ምሳው እራት ይሆነዋል
Modern
ቅን አሳቢ ሰው ጽጌረዳ አበባው ላይ ሲያተኩር፤ ጨለምተኛ ሰው ግን አበባውን በመዘንጋት እሾሁ ላይ ያተኩራል
Classical
አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማም